KUKUNET digital
Architecture

K-CON management

ስለ

ይህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አሠራርን ለማዘመን በኩኩኔት ዲጅታል KUKUNET digital የተዘጋጀው መተግበሪያ በመጋቢት ወር 2015 ዓ.ም. በየካ አያት ቁጥር 2፣ እድገት በአንድነት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማኅበር (ከሕንጻ 04 እስከ 09) ተግባር ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ መተግበሪያው የጋራ ሕንጻዎችን፣ ነዋሪዎችን፣ የጋራ መገልገያ ንብረቶችን በቀላሉ ለመከታተል የሚያግዝ ሲሆን፣ በቀጣይም ነዋሪዎችን በይበልጥ ማስተሳሰር የሚችሉ ተጨማሪ ተግባራትን እንዲይዝ ይደረጋል፡፡ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ከሕጻናት እስከ አዛውንቶች፣ በትምህርት ካልገፉ እስከ ምሁራን፣ ተቀጥረው ከሚሠሩ እስከ ድርጅት ባለቤቶች የሚኖሩበት ትልቅ የማኅበረሰብ ክፍል እንደመሆኑ ሁሉንም ሊያቅፍ የሚችል፣ ዘመናዊ የተደራጀ አገልግሎት የሚሠጥ የአመራር ሥርዓት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህንን ዕውን ለማድረግም በርካታ ጥረቶች የሚደረጉ ሲሆን ይህ መተግበሪያም ከነዚያ ጥረቶች መካከል አንዱ ሆኖ እንዲያገለግል በሚል እሳቤ ተዘጋጅቷል፡፡

ይጻፉልን

እባክዎ የእንግሊዝኛ ፊደሎችን ይጠቀሙ